በምዕራብ ቻይና ቲቤት ማክሰኞ ዕለት በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ 100 ገደማ ሰዎች መሞታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ወደ 1500 የሚጠጉ የእሳት አደጋ እና የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍርስራሹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለመፈለግ መሰማራታቸውን የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ሚኒስቴር አስታውቋል። ...